በጎንደር ከተማ በተካሄደው ውጊያ የሰዎች ህይወት አለፈ
በአማራ ክልል በጎንደር ከተማና አካባቢዋ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ በፋኖ ታጣቂ ቡድንና በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መካከል በነበረ ግጭት “ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሲቪሎች ተገድለዋል” ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በከተማዋ ዙሪያ አይባና ፈንቅጥ በተባሉ ቦታዎች በከተማው ውስጥ ደግሞ በተለምዶ ደሣለኝ፣ ኅዳሴና ሸዋ ዳቦ በሚባሉ አካባቢዎች ካለፈው አርብ ጀምሮ ከባድ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱን ተሰምቷል።
የጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 አካባቢ ነዋሪ እንዳሉት በደኅንነት ሥጋት ምክንያት ማንነታቸውን እንዳንገልፅ የጠየቁ ሰው የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና የፋኖ ታጣቂዎች ካለፈው ሣምንት አርብ ጀምሮ እስከ ትላንት፣ እሁድ ምሽት ድረስ በከተማዪቱ ዙሪያ በሁለት አቅጣጫ ተኩስ መለዋወጣቸውን ጠቅሰዋል። ቀጥሎም የተኩስ ልውውጡ ወደ ከተማዪቱ ዘልቆ መግባቱንና ሲቪሎች መገደላቸውን ተናግረዋል።
ሸዋ ዳቦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደሚኖሩ የገለፁና በተመሳሳይ ምክንያት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ሌላ ነዋሪም በአካባቢው በነበረው የተኩስ ልውውጥ “ጎረቤቶቼን ጨምሮ ሌሎችም ሲቪሎች ተገድለዋል” ብለዋል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሶማሊላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ ጋር በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ መወያየታቸው ተገለጸ
የመከላከያ ሠራዊት በፌስቡክ ገጹ እንዳለው፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላና የሶማሊላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን ውይይት አድርገዋል።
“በሶማሊላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ የተመራ ልዑክ በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ሲደርስ በጄኔራል መኮንኖች አቀባበል ተደርጎለታል” በማለትም ተገልጿል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
በትግራይ የሚንቀሳቀሱ 72 ሲቪል ተቋማት የፌደራል መንግስት በትግራይ ላለው ረሃብ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ሁኔታው እያጣጠለ ነው ሲሉ ወቀሱ
የሴቶች እና ወጣቶች ነፃ ማሕበራት ጨምሮ የተለያዩ የሙያ ማሕበራት እና ሌሎች በአጠቃላይ 72 ሲቪል ማሕበራት ያቀፈው የትግራይ ሲቪል ማሕበረሰብ ተቋማት ሕብረት እንደገለፀው፥ በጦርነት እና በሙሉ መዘጋት የነበረው የትግራይ ህዝብ አሁን ደግሞ ለድርቅ ተጋልጦ፣ በየዕለቱ በርካቶች በረሃብ ምክንያት እየሞቱ ነው ይላል።
በዚህ የሲቪል ማሕበራቱ መግለጫ እና የሌሎች የማሕበረሰብ ተወካዮች ጥሪ ዙርያ ከፌደራል መንግስቱ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
Support Reyot Media:
Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb
Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about
Follow us:
Twitter: @reyotmedia
Facebook: @ReyotMedia
Instagram: @reyot_media
TikTok: @reyotofficial
Threads: @reyot_media
