Connect with us

Hi, what are you looking for?

News

የርዕዮት የዕለቱ ዜናዎች

በአራት ክልሎች ከአራት ሚልዮን በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍን እንደሚያስፈልጋቸው ተነገረ

በአፋር፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ ፣ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች በድርቅ የተጠቁ አካባቢዎች ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንና በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ
እርዳታ አስተባባሪ በኢትዮጵያ አስታወቁ።

ሁለቱ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በተመለከተ በጋራ በሰጡት መግለጫ ድርቁን ተከትሎ ካጋጠመው የምግብ እጥረት ባለፈ በነዚህ
አካባቢዎች እንደ ወባ፣ ኩፍኝና ኮሌራ ያሉ በሽታዎች መከሰትን ጨምሮ በቀንድ ከብቶች ላይም ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ገልጸዋል። ያለው ስር የሰደደ የሃብት ውስንነት እንዳለ ሆኖ ድጋፎቹን በሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ለማዳረስ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚያጋጥመው የጸጥታ ችግር የሰብዓዊ እርዳታ የማከፋፈሉ ስራ ላይ አሉታዊ ጫና ማሳረፉም መግለጫው አመላክቷል።

መንግሥት በወሰደው እርምጃ 2 ቢልዮን ዶላር ገደማ መክሰሩ ተሰማ

የአለም አቀፍ የቪፒኤን ግምገማ ድረ-ገጽ ቶፕ10ቪፒኤን በ2023 የኢትዮጵያ መንግስት ባደረገው የኢንተርኔት መዝጋት እና የማህበራዊ ሚዲያ እገዳዎች ምክንያት አገሪቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ሁለተኛውን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ኪሳራ እንደደረሰባት የሚያሳይ ዘገባ አሳትሟል።

የኢትዮ ጁቡቲ ተመላላሽ ከባድ ተሸከርካሪዎች መቃጠላቸው ቅሬታ አስነሳ

የኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር በዚህ ሳምንት በምሥራቅ ሸዋ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት አራት የጭነት መኪኖች መቃጠላቸው በአሽከርካሪዎች ላይ በተደጋጋሚ የሚፈፀመው ግድያ፣ እገታና የቤዛ  ጥየቃ አካል ነው አለ።

የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ለጥቃቱ የኢትዮጵያ መንግስት ኦነግ ሸኔ በሚል ስያሜ በአሸባሪነት የፈረጀዉን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊቲን ተጠያቂ አድርጓል።

ማህበሩ ከዚህ በፊትም ይኽ ችግር በመደጋገሙ ከኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ኤጀንሲ እና ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ጋር መፍትሔ ፍለጋ ውይይት ማድረጉ ይታወሳል። ይህ ችግር መልኩን ቀይሮ ወደ እገታ እና ቤዛ ወይም ማስለቀቂያ ገንዘብ ጥየቃ ከመሻገሩ አልፎ አሁን ተሽከርካሪዎችን እና የጫኑትን ንብረት ወደማቃጠል በመገባቱ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት በደብዳቤ ተጠይቋል ተብሏል።

በሶማሊያና ሶማሊላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጥቃት እየደረሰባቸው ነው ተባለ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ የባሕር ጠረፍ ያስገኛል የተባለውን የመግባቢያ ሠነድ መፈራረማቸውን ተከትሎ በሶማሊያ እና ሶማሊላንድ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ አካላዊ ጥቃት እና የንብረት ዝርፊያዎች እየተፈጸሙ መሆኑን እንዲሁም ማስፈራሪያዎች
እየደረሱ እንደሆነ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ተናገሩ።

በተለይ በሶማሊላንድ በኢትዮጵያውያን ላይ አካላዊ ጥቃት መፈጸሙን፣ ንብረታቸው መዘረፉን እና መኖሪያ ቤታቸውን ለማቃጠል ሙከራ መደረጉን የስደተኞች ተወካይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በሶማሊያም በኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት እንዲፈጸም የሚጠይቁ ቅስቀሳዎች መኖራቸውን ኢትዮጵያውያኑ ተናግረዋል።

ኦነግ የሶማሊላንድና ኢትዮጵያ ስምምነት ቃጠናውን የሚያውክ ነው ሲል ገለጸ

ኦነግ የኢትዮጵያ መንግስት እና የሶማሊላንድ ራስ-ገዝ አስተዳደር የፈረሙት የመግባቢ ሰነድ በቃጣናው የውጥረት መንገስ ምክንያት እንዳይሆን ያሰጋል አለ፡፡ በአከባቢው ሁሉም አካላት ውጥረቱን በሰከነ አካሄድ እንዲፈቱት በጠየቀበት በዚሁ መግለጫ፤ ኦነግ በተለይም ለስደተኞች እና ሰላማዊ ዜጎች ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባ ነው ያሳሰበው፡፡

ፓርቲው በመግለጫው ከዚህ በፊትም የሁለቱ አገራት መንግስታት በፈጠሩት እሰጣ ገባ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተለይም ሶማሊያ ውስጥ በተጠለሉ የኦሮሞ ስደተኞች ላይ በታሪክ አጋጣሚ ተደጋጋሚ ጥቃት መሰንዘሩን አስታውሷል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ከጎረቤት የሶማሊያ ህዝብ ጋር ለዘመናት ባህል፣ ወግ፣ ሃይማኖት እና ድንበር ተጋርቶ በሰላም መኖሩን ያወሳው ኦነግ በገዢዎች ተደጋግሞ በሚቀሰቀስ ግጭት ግን የሰው ህይወት እና ሃብት ስወድም መቆየቱንም አመልክቷል፡፡ ፓርቲው በመግለጫው
በኦነግ እና ወንድም ህዝብ ባለው የሶማሊያ ህዝብ መካከል ለፍትህ እና ሰብኣዊ መብት መከበር ያደላ አዎንታዊ ግንኙነት መኖሩንም ገልጾ የጋራ ሰብኣዊ እሴት ያለው ይህ ግንኙነት እንዳይበላሽ የሶማሊያ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የአገር
ሽማግሌዎች እና ህዝብ አንቂዎች ጥሪ እንዲያሰሙም ጠይቋል፡፡

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የ2 ቀን የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመልሰዋል

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ በኤርትራ ያደረጉትን የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ወደ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በሁለትዮሽ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት መወያየታቸውን የኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር አስታውቋል። ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ እንዲሁም በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ከግጭት ቀስቃሽ አጀንዳዎች በመቆጠብ በጋራ ለመስራት
ተስማምተዋል።

የኤርትራ መንግስት ከላይ በተገለጹት የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በቅርቡ ሰፊ መግለጫ እንደሚያወጣም አስታውቋል።

Support Reyot Media:

Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb

Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about

Follow us:

Twitter: @reyotmedia

Facebook: @ReyotMedia

Instagram: @reyot_media

TikTok: @reyotofficial

Threads: @reyot_media

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Trending

You May Also Like

Sticky Post

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ትውልድ ይፈርድብናል አሉ በትናትናው እለት በተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተገኝተው ንግግር ያሰሙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመረቀው ሙዚየም አገርን ለሆነው ላልሆነውማናወጥ፤...

Sticky Post

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች እና የህወሓት ከፍተኛ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ተገናኙ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል...

Sticky Post

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹም ሽር አደረጉ በዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ የሶስት ሚኒስትሮች ሹመት ጸደቀ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሥልጣን የተሰናበቱትን ምክትል ጠቅላይ...

Sticky Post

ምክር ቤቱ ይፋዊ ይቅርታ ለመጠየቅ መቐለ ገባ በ ሸኽ ሓጂ ሙሐመድ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን...