ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹም ሽር አደረጉ
በዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ የሶስት ሚኒስትሮች ሹመት ጸደቀ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሥልጣን የተሰናበቱትን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን በመተካት አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሹመዋል።
እንዲሁም በቀድሟዋ የጤና ሚኒስቴር ሊያ ከበደ ስፍራ ዶክተር መቅደስ ዳባ ተሹመዋል።
ሲቪል ማህበራት በሚካሄዱ ድርድሮች አካታችነት ላይ ጥያቄ አነሱ
በኢትዮጵያ የሚገኙ ሲቪል ማህበራት በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ባወጡት መግለጫ ሴቶች በግጭቶ በግንባር ቀደምትነት ተጠቂዎች እንደመሆናቸው የሚደረጉ የሰላም ድርድሮች ሴቶችን ማሳተፍ እንደሚገባቸው በአጽንዖት አሳስበዋል።
እስካሁን በተደረጉት የፕሪቶሪያ እና የታንዛኒያ ንግግሮች ሴቶች አለመሳተፋቸውን አውስተው መንግሥትም ሆነ ሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሴቶችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሊወስኑ በሚችሉ ውይይቶች ላይ አካታችነት መኖሩን እንድያረጋግጡ ጠይቀዋል።
በነቀምት ያለው አለመረጋጋት ህዝቡን ስጋት ላይ ጥሏል ተብሏል
በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የገበያ እና የመጓጓዣ አድማ ከጠራ 10 ቀናት በኋላ
የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች መዳረጋቸውን ተሰማ።
ነዋሪዎቹ እንዳሉት አድማው በክልሉ በአብዛኛው አካባቢ ቢያበቃም በነቀምቴ ከተማ ግን አሁንም ድረስ መቀጠሉ ለከፋ ችግር አጋልጧቸዋል።
የተላለፈውን አድማ ተባብራችኋል በሚል በመንግሥት ባለሥልጣናት በተሽከርካሪ እና በኦሮሚያ የቀጠለው የጸጥታ ስጋት በንግድ ተቋማት ባለቤቶች ላይ እየወሰዱ ያሉት አስተዳደራዊ እርምጃዎች ችግሩ በከተማዋ እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል።
የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከአራት ቀናት በፊት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ « አሸባሪው የሸኔ ቡድን የሽብር ተግባሩን አጠናክሮ በመቀጠል የክልሉን ሰላም እና መረጋጋት ለማናጋት የመጓጓዣ እና የገበያ ዕቀባ ቢጠራም በመንግሥት እና በህዝብ ተሳትፎ ከሽፏል » ብሎ ነበር።
ነገር ግን የነቀምቴ ከተማን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የየብስ የመጓጓዛ አገልግሎቶች ከታጣቂዎች የሚሰነዘር ጥቃትን ሽሽት መስተጓጎላቸውን ከየአካባቢው መረጃዎች ያመለክታሉ።
Support Reyot Media:
Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb
Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about
Follow us:
Twitter: @reyotmedia
Facebook: @ReyotMedia
Instagram: @reyot_media
TikTok: @reyotofficial
Threads: @reyot_media