Connect with us

Hi, what are you looking for?

News

የርዕዮት ዜናዎች፤ 04 – የካቲት – 2016

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ትውልድ ይፈርድብናል አሉ

በትናትናው እለት በተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተገኝተው ንግግር ያሰሙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመረቀው ሙዚየም አገርን ለሆነው ላልሆነው
ማናወጥ፤ የአገርን ዝና ማበላሽት ሳይሆን የአገር ፍቅርን የሚቆረቁር መሆን አለበት ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ልዩነትለመፍታት ቃታ መምዘዝ የሚቀለን ሆነናል ያሉት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ትውልድ ይፈርድብናል ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

መንግስት ከፍተኛ የሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ወሰድኩ አለ

መንግስት በምስራቅ ወለጋ ዞን በሸኔ ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ የቡድኑ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ጃን ፈልመታ እና ጃን ሌንጮን ጨምሮ ከስልሳ በላይ የሚሆኑ የቡድኑ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱ የተገለፀ ሲሆን በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችና ተተኳሾች መማረካቸውንም ተዘግቧል።

የምስራቅ ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ገመዳ ተፈራ፣ ሰራዊቱ ለአካባቢው ሰላም መረጋገጥ በየጊዜው እየከፈለ ባለው የህይወት መስዋዕትነት ጭምር የአካባቢውን ሰላም ማረጋገጥ መቻሉን ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ነጻነት ሰራዊት በበኩሉ መንግስት ወሰድኩት ላለው እርምጃ እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም።

በደቡብ ወሎ ማዕድን ሲያወጡ ናዳ የተጫናቸውን በርካታ ሰዎች የማዳን ጥረት አራተኛ ቀኑን ያዘ

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ፣ ደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ ሳሉ ዋሻ የተደረመሰባቸውን በርካታ ሰዎች ለማውጣት የሚደረገው ጥረት አራተኛ ቀኑን ይዟል።

የአካባቢው ባለሥልጣን እና የከበረ ማዕድን አውጪዎች ማኅበር ሊቀመንበር ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቁጥር ከ8 እስከ 30 የሚገመቱትን ሰዎች ለማውጣት የአካባቢው ማህበረሰብ ጥረት እያደረገ ቢሆንም እስካሁን ውጤት አልተገኘም።

ሐሙስ ጥር 30/2016 ዓ.ም. ምሽት 3፡00 አካባቢ የተከሰተ ናዳ በሕጋዊ መንገድ ተሰማርተው በማዕድን ቁፋሮ ላይ የነበሩት ሰዎች ናዳ የተጫናቸው ሲሆን ተጨማሪ የአካባቢው ወጣቶችም አብረው ሳይኖሩ እንዳልቀረ ተነግሯል።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አያሌው በሪሁን ባለፉት ቀናት ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች በነፍስ አድን ሥራው ላይ እገዛ ለማድረግ ወደ ሥፍራው ቢያቀኑም፣ ወደ ዋሻው ለማምራት የሚያስችለው መንገድ ጠባብ እና በአንድ ጊዜ ከአስር ሰዎች በላይ ማስገባት ባለመቻሉ ጥረታቸው አዝጋሚ መሆኑን ተናግረዋል።

ስምንት አባላቱ በናዳው ተይዘው እንደሚገኙ የገለጸው ወርቅ ዋሻ የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማህበር ሊቀመንበር ተስፋዬ አጋዥ በበኩላቸው እስካሁን በተደረገው ጥረት 150 ሜትር ርዝማኔ ወዳለው ዋሻ ዘልቆ ለመግባት መቆፈር የተቻለው 33 ሜትር ገደማ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

ሶማሊያ የአፍሪካ ህብረትና ተመድ በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተደረሰውን ስምምነት እንዲያወግዙ ጠየቀች

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የደረሱትን የመግባቢያ ሰነድ እንዲያወግዙ ጠየቀ።

ስምምነቱ ህገወጥ ነው ሲል በድጋሚ የገለጸው የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ
የሶማሊያን ሉዐላዊነት እና ግዛታዊ አንደነት የጣሰ ነው ብሏል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ተግባር ከብዙ አስርት አመታት በኋላ ቀጠናው ለመረጋጋት እና ሰላም ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሲል መግለጫው አትቷል። እንደ አፍሪካ ህብረት መቀመጫነቷ ህብረቱ የተመሰረተለትን የአህጉሩን ሀገራት አንድነት፣ ሉአላዊነት እና የግዛት አንድነት ማስጠበቅ መርህ ከማስከበር ይልቅ በመጣስ የህብረቱን ህልውና ስጋት ላይ የሚጥል ተግባር ፈጽማለች ብሏል።

ሶማሊላንድ በበኩሏ መግለጫው ተቀባይነት የለውም ስትል ተችታለች።

Support Reyot Media:

Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb

Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about

Follow us:

Twitter: @reyotmedia

Facebook: @ReyotMedia

Instagram: @reyot_media

TikTok: @reyotofficial

Threads: @reyot_media

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Trending

You May Also Like

Sticky Post

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች እና የህወሓት ከፍተኛ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ተገናኙ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል...

Sticky Post

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹም ሽር አደረጉ በዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ የሶስት ሚኒስትሮች ሹመት ጸደቀ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሥልጣን የተሰናበቱትን ምክትል ጠቅላይ...

Sticky Post

ምክር ቤቱ ይፋዊ ይቅርታ ለመጠየቅ መቐለ ገባ በ ሸኽ ሓጂ ሙሐመድ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን...

Sticky Post

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በረሀብ የሞተ ሰው የለም አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማራሪያ በአገሪቱ በረሀብ የሞተ ሰው የለም...