የግብጽ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር በኤርትራ ጉብኝት አደረጉ
የግብጽ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሜህ ሹክሪ የፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲን መልዕክት ይዘው አስመራ ገብተዋል። በትናንትናው እለት ምሽትም የኤርትው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሜህ ሹክሪ የተመራውን የግብጽ ልዑክ ተቀብለው ማነጋገራቸውን የሀገሪቱ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚሁ ወቅትም የግብጽ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሜህ ሹክሪ ከፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲን የተላከውን ደብዳቤ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አድርሰዋል። የፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ ደብዳቤም “የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማጠናከር እና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት” ላይ የሚያተኩር መሆኑ ተነግሯል።
ኢጋድ በኢትዮጵያና ሶማሊያ ለመወያየት አስቸኮይ ስብሰባ ጠራ
የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውዝግብ ዙሪያ ለመነጋገር አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ተሰምቷል።
የወቅቱ የኢጋድ ሊቀ መንበር የሆኑት የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ የጠሩት ይህ ስብሰባ በኡጋንዳ እንደሚካሄድና ትኩረቱም በኢትዮጵያና ሶማሊያ ሰሞነኛ ውዝግብ እና በሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ላይ እንደሚሆን ታውቋል።
መንግሥት የተቃውሞ መልዕክት አለው ያለውንቲያትር አገደ
በዓለም ሲኒማ ሲታይ የነበረው የእያዩ ፈንገስ “ቧለቲካ” ቴአትር መታገዱ ተሰምቷል።
በአዲስ አበባ ላለፉት ሁለት ወራት ሲታይ የነበረው “ቧለቲካ” ቴአትር መታገዱን የአዘጋጆቹ የቅርብ ሰዎች አረጋግጠዋል። ቴአትሩ የታገደው “የመንግሥት ሰዎች ነን” የሚሉ በሰጡት ትዕዛዝ እንደሆነ ጉዳዩን በቅርብ ያውቃሉ የተባሉ ምንጮች ተናግረዋል።
የአማራ ክልል የሰላም እጦት እንዳሳሰበው የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ
በአማራ ክልል በተፈጠረው ግጭት 61 የጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወድመው 39ኝ ላይ ከፊል ጉዳት በመድረሱ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ መስተጓጎሉን የአለም የጤና ድርጅት አመለከተ። በማከልም በእንቅስቃሴ ላይ የሚደረጉ ገደቦች የሰብአዊ እርዳታን ለማድረስ እንቅፋት መሆናቸዉን ገልጿል።
በተጨማሪም በትግራይ እና አማራ ክልሎች የተከሰተው ርሃብ እና እነዚህን ክልሎች ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ ከ30,000 በላይ ሰዎችን በኮሌራ በሽታ መጠቃታቸው አሳሳቢ እንደሆነ ድርጀቱ አስታውቋል።
የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጉሕዴን) አባላቱ እንደታሰሩ መሆናቸዉን አስታወቀ
በበኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሰዉ የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጉሕዴን) አምና ጥቅምት ከክልሉ መንግስት ጋር ባደረገዉ ስምምነት መሠረት የታሰሩ አባላቱ መለቀቅ የነበረባቸው ቢሆንም ከ190 የሚበልጡ አባላቱ አሁንም እንዳታሩ መሆናቸውን ገልጿል።
የክልሉ የፍትሕ ቢሮ በበኩሉ ፓርቲዉ ታስረዋል ያላቸዉን ሰዎች ቁጥር የተጋነንና እስር ቤት የሚገኙትም ጉዳያቸዉ በማጣራት ሂደት ላይ ነዉ ብሏል።
በአማራ ክልል በረሀብ ምክንያት ሰዎች እየተፈናቀሉ መሆኑን ተገለጸ
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከአራት ሺ በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ከቀያቸውን ለቀው ወደ ከተሞች መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።
በሁለቱ ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ከ86 ሺ በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸውን እና ከ173 ሺህ በላይ መሰደዳቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።
ድርቁ ባስከተለው ረሃብ ምክንያት አራት ቀን በእግር ተጉዘው በአጎራባቹ ዓድ ዓርቃይ ከተማ እንደሚገኙም ተዘግቧል።
Support Reyot Media:
Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb
Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about
Follow us:
Twitter: @reyotmedia
Facebook: @ReyotMedia
Instagram: @reyot_media
TikTok: @reyotofficial
Threads: @reyot_media