Connect with us

Hi, what are you looking for?

News

የርዕዮት ዜናዎች፡ ጥር – 04 – 2016

በጎንደር ከተማ የሚካሄደው ውጊያ አሁንም ቀጥሏል

በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በቀናት ልዩነት ለሁለተኛ ጊዜ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ገለጹ።

ሐሙስ ጥር 2፤ 2016 ዓ.ም ከ5፡00 ሰዓት ገደማ ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ በዘለቀው የተኩስ ልውውጥ፤ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች በመሣሪያ መመታታቸውን ሁለት ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የአካባቢው ነዋሪ እንደተናገሩት፤

 4፡40 ሰዓት አካባቢ የፋኖ ኃይሎች እዚህ ገብተዋል በሚል የመንግስት ሚሊሻ እና መከላካያ፤ ከባባድ መሣሪያዎችን የታጠቁ የመንግስት ኃይሎች ወደ ከተማዋ በመግባት ተኩስ ከፈቱ።

ቢቢሲ አማርኛ

እንደ ነዋሪው ገለጻ የተኩስ ልውውጡ የተጀመረው የሰዎች እና የንግድ እንቅስቃሴ በነበረበት የሥራ ሰዓት በመሆኑ ነዋሪዎች ላይ ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር።

ሐሙስ ዕለት የተኩስ ልውውጥ መጀመሩን ተከትሎ በከተማዋ የሚደረገው እንቅስቃሴ ቆሞ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎቹ አርብ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ሁኔታዎች ወደ ነበሩበት መመለሳቸውን ተናግረዋል።

ጎንደር ከተማ በቀናት ልዩነት ውስጥ የፋኖ ኃይሎች እና በመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የሚደረግን የተኩስ ልውውጥ ስታስተናግድ የሐሙሱ ለሁለተኛ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ እና እሁድ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከ20 በላይ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተዘግቦ ነበረ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን መንግሥት ጣልቃ እየገባብኝ ነው ስትል ከሰሰች

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ የሚወጣ ነገር በሙሉ በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ይፈተሻል ሲሉ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተከህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳር አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ትናንት በሰጡት መግለጫ መንግስትን ከሰሱ።

አቡነ አብርሃም፣ ድርጊቱ ቤተክርስቲያኗን መድፈር መሆኑን ገልጸዋል። የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ፍተሻ የሚያካሂዱት፣ ሰሞኑን አንድ ጳጳስ ለተናገሩት ንግግር ቤተክርስቲያኗ መንግሥት የፈለገውን ምላሽ ባለመስጠቷ ነው ብለዋል።

ቤተክርስቲያኗ ጥምቀት በዓልንም ለማክበር መጀመሪያ የጳጳሱን ንግግር እንድታወግዝ መንግሥት መጠየቁን የጠቀሱት አቡነ አብርሃም፣ ቤተክርስቲያኗ ግን የራሷን ሕጋዊ አካሄድ እንጂ የማንንም ትዕዛዝ አትቀበልም ብለዋል።

በተጨማሪም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጼጥሮስ ከአገር ኮብልለዋል የሚባለው ወሬ ሐሰት መኾኑንና ጳጳሱ ወደ ውጭ አገር ከተላኩበት የቤተክርስቲያኗ አገልግሎት በቅርቡ እንደሚመለሱም አቡነ አብርሃም ገልጸዋል።

ሂውማን ራይትስ ዎች የአውሮፓ ህብረትን ወቀሰ

ሂውማን ራይትስ ዎች አዲስ ባወጣው የዓለም የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ተጠያቂነት እንዲሰፍንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ወደሚያስችሉ ዓለማቀፋዊ እርምጃዎች አላመራም በማለት ተችቷል።

በአማራና ትግራይ ክልሎች በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችና ሌሎች ጥሰቶች ቀጥለዋል ያለው ድርጅቱ፣ አውሮፓ ሕብረትና ሌሎች ምዕራባዊያን አገራት ግን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ግንኙነታቸውን እንደገና ጀምረዋል በማለት ወቅሷል።

የኤርትራ ታደሮች በትግራይ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዳይደርስ እንደሚያደናቅፉና በአማራ ክልልም ውጊያ፣ የቴሌኮምንኬሽን መቋረጥና በረድኤት ሠራተኞች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ለዕርዳታ ሥርጭት እንቅፋት እንደሆኑ ሪፖርቱ ጠቅሷል።

የትግራይ ክልል የፌደራል መንግስት ለልማታዊ እንቅስቃሴዎች ድጋፍ እያደረገ አይደለም ሲል ወቀሰ

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጎዳው የትግራይ ክልል የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማነቃቃትና የወደሙትን ፋብሪካዎች መልሶ ለመገንባት ለሚያደረገው ጥረት የፌዴራሉ መንግሥት፣ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያደርግ የትግራይ ክልል የኢንዱስትሪ ቢሮ ጠይቋል፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መሐሪ ገብረ ሚካኤል ከጦርነቱ በፊት በትግራይ የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች አብዛኞቹ በጦርነቱ መጎዳታቸውን ተናግረዋል፡፡ የፕሪቶርያውን ስምምነት ተከትሎ፣ በክልሉ ሰላም ቢፈጠርም፣ የኢንዱስትሪ ዘርፉን መልሶ ለመገንባት የፌዴራሉ መንግሥት በቂ ድጋፍ እያደረገ አይደለም ብለዋል፡፡

ዘርፉን በማነቃቃት በክልሉ ያለውን ድህነት እና ሥራ አጥነት ለመቀነስ እንዲቻልም፣ መንግሥት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያደርግ አቶ መሐሪ ጠይቀዋል፡፡

በሶማሊያ ዋና ከተማ የሞርታር ጥቃት የተመድ ሰራተኛን ህይወትን ቀጥፏል

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቋዲሹ ትናንት ምሽት በደረሰ የሞርታር ጥቃት የተባበሩት መንግስታት የጥበቃ ክፍል አባል በአሳዛኝ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል።

በሶማሊያ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ተልዕኮ ( UNSOM) ጥቃቱን አጥብቆ አውግዞ ለተጎጂው ቤተሰ ብ እናየስራ ባልደረቦች ሃዘኑን ገልጿል።

ጥቃቱ የተፈጸመው የተባበሩት መንግስታት ግቢ በሚገኝበት አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ ነው። ጥቃቱ ከጠፋው የሰው ህይወት በተጨማሪ በመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተዘግቧል።

ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን ለጥቃቱ ሃላፊነቱን ወስዷል። ተመድ ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ የጠየቀ ሲሆን የሶማሊያ ህዝብ እና መንግስት ሰላምና መረጋጋትን ለመፍጠር በሚያደርጉት ጥረት ድጋፍ ለማድረግ ያለውንም ቁርጠኝነት አረጋግጧል።

Support Reyot Media:

Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb

Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about

Follow us:

Twitter: @reyotmedia

Facebook: @ReyotMedia

Instagram: @reyot_media

TikTok: @reyotofficial

Threads: @reyot_media

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Trending

You May Also Like

Sticky Post

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ትውልድ ይፈርድብናል አሉ በትናትናው እለት በተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተገኝተው ንግግር ያሰሙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመረቀው ሙዚየም አገርን ለሆነው ላልሆነውማናወጥ፤...

Sticky Post

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች እና የህወሓት ከፍተኛ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ተገናኙ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል...

Sticky Post

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹም ሽር አደረጉ በዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ የሶስት ሚኒስትሮች ሹመት ጸደቀ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሥልጣን የተሰናበቱትን ምክትል ጠቅላይ...

Sticky Post

ምክር ቤቱ ይፋዊ ይቅርታ ለመጠየቅ መቐለ ገባ በ ሸኽ ሓጂ ሙሐመድ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን...