በድሮን ጥቃት ተማሪዎች ተገደሉ
በአማራ ክልል መርሐቤቴ ወረዳ ከአንድ ትምህርት ቤት አቅራቢያ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ቢያንስ አራት ሰዎች እንደቆሰሉ ነዋሪዎች እና የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ገለጹ።
በሰሜን ሸዋ ዞን በምትገኘው መርሐቤቴ ወረዳ ዓለም ከተማ የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ዓርብ ጥር 3/2016 ዓ.ም. መሆኑን ሦስት ነዋሪዎች እና የትምህርት ቤቱ አስረድተዋል።
ከቀኑ ሰባት ሰዓት ገደማ የተፈጸመው ጥቃት ያረፈው አርበኞች አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መግቢያ አካባቢ መሆኑ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ አሻግሬ አበበ ተናግረዋል።
ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚያስረዱት በትምህርት ቤቱ አቅራቢያ ጥቃቱ የተፈጸመው በአካባቢው በሚገኘው “ካርል” የተባለ መናፈሻ ውስጥ የፋኖ ታጣቂዎች ይገኛሉ በሚል ነው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር ሂደቶችን ለማከናወን ዝግጅት እየደረገ መሆኑን አሳወቀ
ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሀገራዊ ምክክር ሂደቶችን ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ነፍጥ ያነሱ ወገኖች በሰላማዊ መንገድ ወደ ምክክሩ እንዲመጡ መንግስት ለሰላማዊ አማራጭ ቅድሚያ ሰጥቶ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ረገድ የበለጠ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።
ቀደም ብሎ የምክክር ኮሚሽኑን በተመለከተ በሩቅ ሆነው ቅሬታ ሲያነሱ የነበሩ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ ግን የኮሚሽኑን ትክክለኛ ተልዕኮ በቅርበት በመረዳት በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገራዊ ምክክር ስኬት በጋራ ለመስራት መግባባት መፍጠራቸውን ገልጸዋል።
ኮሚሽኑ እንደ ገለልተኛ ተቋም ከሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በጋራ መስራት እንደሚፈልግ ገልጸው፣ ኮሚሽኑ በሲዳማ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሀረሪ፣ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች የተሳታፊ ልየታ ማካሄዱን አስታውሰዋል። ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ልየታ ያላካሄደ ሲሆን በክልሉ ያለው እቅድ ሳያሳውቅ ቀርቷል።
በትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች በእርዳታ አቅርቦት እጥረት ለሞትና በሽታ እየተጋለጡ መሆኑ ተናገሩ
በሽረ፣ ዓብይአዲ፣ መቐለ ያሉ የትግራይ ጦርነት ተፈናቃዮች መንግስት ወደቀዬአቸው እንዲመልሳቸው እንዲሁም ዓለምአቀፍ ለጋሾችም የእርዳታ እጃቸው እንዲዘረጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል። እንደ ክልሉ አስተዳደር መረጃ በትግራይ አንድ ሚልዮን ገደማ ተፈናቃዮች በትምህርት ቤቶች፣ ግዚያዊ መጠልያ ሸራዎች እንዲሁም ቤተእምነቶች እና ሌሎች ስፍራዎች ተበትነው ይገኛሉ።
ተፈናቃዮች ጦርነቱ ከቆመ ከ15 ወር በኋላ በሚበላ ምግብ እና የሚጠጣ ውሃ እጦት እየተሰቃዩ መሆኑንና ለበሽታ መዳረጋቸውንም ተናግረዋል። ለክልሉ አስተዳደር እና ለፌደራል መንግስቱ ወደቀዬአቸው ለመመለስ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ተግባራዊ ምላሽ የለም ይላሉ።
የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የጦርነቱ ተፈናቃዮች በፕሪቶሪያው ውል መሰረት ወደቀዬአቸው እንዲመለሱ በተደጋጋሚ እያወጣቸው በነበረ መግለጫ ሲጠይቅ ነበር። የፌደራሉ መንግስት በተፈናቃዮቹ ያለው አቋም እስካሁን አላሳወቀም።
Support Reyot Media:
Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb
Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about
Follow us:
Twitter: @reyotmedia
Facebook: @ReyotMedia
Instagram: @reyot_media
TikTok: @reyotofficial
Threads: @reyot_media