Connect with us

Hi, what are you looking for?

News

የርዕዮት ዜናዎች፡ 07- ጥር -2016

የቱርክ መንግስት አልነጃሲ መስጅድን ለማደስ ጥያቄ አቀረበ

የቱርክ መንግሥት፣ ትግራይ ክልል የሚገኘውን የአል-ነጃሲን መስጅድ ለማደስ መጠየቁን፣ የቅርሥ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።

መነሻውን በትግራይ ክልል ባደረገው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ መስጅዱ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር ያስታወሱት የተቋሙ ዋና ዲሬክተር አቶ አበባው አያሌው፣ የቱርክ መንግሥት መስጅዱን መልሶ ለመጠገን መጠየቁንና በእድሳቱ ዙሪያም ጥናት እንደሚደረግ
አመልክተዋል።

በጦርነቱ ትግራይ ክልል በሚገኙ ቅርሶች ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን ለማወቅም ተቋማቸው ጥናት ማካሔድ መጀመሩን ሓላፊው ጨምረው ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ልዩነትን የሚያጠብ ምክር ከሀይማኖት አባቶች እንደሚጠብቁ ተናገሩ

በሽረ እንዳስላሰ በድምቀት ተከብሮ የዋለው የስላሴ አመታዊ ሀይማኖታዊ ክብረበዓል ላይ የተገኙት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ አንድነታችንን አጠናክረን ትግራይን እንገንባ ብለዋል፡፡

በትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለስና በክልሉ ያለው ያልተሟላ ሰላም ሙሉ ለማድረግ መስራት ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ ከሃይማኖት አባቶች ልዩነታችሁን ወደ ጎን አድርጋችሁ ለምታምኑት ተገዢ ሁኑ የሚል ምክራ እንጠብቃለን ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ በሽረ እንዳስላሴ የጸሀየ ትምህርት ቤት የሚገኙ የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን የጎበኙ ሲሆን፤ የትግራይ ህዝብ እያለፈው ያለው ስቃይና መከራ ልብ የሚሰብር ነው ብለዋል፡፡ ተፈናቃዮቹን ወደ ቀያቸው ለመመለስና የትግራይ ግዛቶችን ለመመለስ አስተዳደሩ ይሰራል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የፌደራሉ መንግሥት ቃሉን አጥፏል አለ

በአማራ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጊዜው ሳይደርስ ሊነሳ እንደሚችል መንግስት ቃል ገብቶለት የነበረ ቢሆኖም አሁንም ክልሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር መሆኑን የአውሮፓ ህብረት አስታውቋል፡፡

በህብረቱ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሮላንድ ካቢያ ለአል ዐይን እንዳሉት፤

“ኢትዮጵያ ከትግራይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደ ሌላ አስቸኳይ አዋጅ በመግባቷ እናዝናለን፣ በአማራ ክልል የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለስድስት ወራት እንዲቆይ ተደርጎ ታወጀ እንጂ ጊዜው ከመድረሱ በፊት እንደሚነሳ በኢትዮጵያ መንግስት ተነግሮን ነበር። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት እኛ እና አጋሮቻችን ስራችንን እንደልብ ተንቀሳቅሰን እንዳንሰራ
አድርጓል፣ መንግስትም የአማራ ክልል ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱን በመናገሩ ምክንያት አዋጁን ለተጨማሪ ጊዜ ያራዝማል የሚል ግምት የለኝም።”

አል ዐይን አማርኛ

በርካታ ኢትዮጵያዊን በጦርነት እና መፈናቀል እየተፈተኑ ነው ያሉት አምባሳደር ሮላንድ ካቢያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲታወጅ የዜጎች መብቶች ከመገደብ አልፎ ለእንግልት እንዲዳረጉ በር ይከፍታልም ብለዋል፡፡

የአረብ ሊግ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ጉዳይ ለውይይት ሊቀመጥ ነው

ኢትዮጵያ በኤደን ባህረ ሰላጤ 20 ኪሎሜትሮች የሚረዝም የባህር ጠረፍ እንድትከራይ እና በምትኩ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና እንድትሰጥ የሚያስችል ነው መግባባያ ሰነድ መፈራረማቸውን ተከትሎ የአረብ ሊግ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጉዳዩ እንደሚመክር
አስታውቋል።

በበይነ መረብ እንደሚካሄድ የተገለጸው ይህ የሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባ የፊታችን ረቡዕ እንደሚካሄድ የሊጉ ምክትል ጸሃፊ ሆሳም ዛኪ ተናግረዋል፡፡ ይህ የሚኒስትሮች ጉባኤ በሶማሊያ ጠያቂነት እንደተጠራ ሲገለጽ ስብሰባው በሊጉ 12 አባላት ድጋፍ እንዳገኘም ተገልጿል፡፡

ኢጋድም በስምምነቱ ዙሪያ ለመመካከር አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ መዘገባችን ይታወሳል።

ኬንያ ለኢትዮጵውያን የመግቢያ ቪዛ ልትጠይቅ ነው

የኬንያ መንግስት ሐገሪቱን ለሚጎበኙ ኢትዮጵያዉያን መንገደኞች አዲስ የመግቢያ ፈቃድ ማጣሪያ ደንብ (Visa Waiver) አዉጥቷል። ሁለቱ ሐገራት ከብዙ ዓመታት በፊት ባደረጉት ስምምነት መሠረት ከአንዱ ሐገር ወደ ሌላዉ የሚጓዝ መንገደኛ የመግቢያ ፈቃድ
(Visa) አያስፈልገዉም ነበር።

የኬንያ መንግስት አዲስ ባወጣዉ ደንብ መሠረት ግን ከፈረንጆቹ 2024 ጀምሮ ወደ ኬንያ የሚገቡ ኢትዮጵያዉያን መንገደኞች ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኦን-ላይን ፎርም መሙላት አለባቸዉ።

ኬንያ ነባሩን ሕግ የቀየረችበት ምክንያት በዝርዝር አልጠቀሰም።ኢትዮጵያ መንግስትም ነባሩን ደንብ ስለመቀየር-አለመቀየሩ አላስታወቀም።

Support Reyot Media:

Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb

Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about

Follow us:

Twitter: @reyotmedia

Facebook: @ReyotMedia

Instagram: @reyot_media

TikTok: @reyotofficial

Threads: @reyot_media



Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Trending

You May Also Like

Sticky Post

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ትውልድ ይፈርድብናል አሉ በትናትናው እለት በተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተገኝተው ንግግር ያሰሙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመረቀው ሙዚየም አገርን ለሆነው ላልሆነውማናወጥ፤...

Sticky Post

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች እና የህወሓት ከፍተኛ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ተገናኙ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል...

Sticky Post

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹም ሽር አደረጉ በዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ የሶስት ሚኒስትሮች ሹመት ጸደቀ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሥልጣን የተሰናበቱትን ምክትል ጠቅላይ...

Sticky Post

ምክር ቤቱ ይፋዊ ይቅርታ ለመጠየቅ መቐለ ገባ በ ሸኽ ሓጂ ሙሐመድ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን...