የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በሶማሊያ እንዳያልፍ ተከለከለ
ወደ ሶማሊላንድ መዲና ሃርጌሳ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የሶማሊያ አየር ክልል ውስጥ ከመግባቱ በፊት እንዲመለስ ተደረገ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እንደተናገሩት ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ሃርጌሳ ሲጓዝ የነበረው አውሮፕላን ከሶማሊያ በኩል ፍቃድ የለውም በመባሉ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ለማረፍ ተገዷል።
የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ዘግይቶ በወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ8372 ፍቃድ ስላልነበረው ሃርጌሳ ላይ እንዳያርፍ መከልከሉን አስታውቋል።
የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይሳ አሮፕላኑ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን የያዘ እንደነበረ ተናግረዋል።
የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንም ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ከተደረገው አውሮፕላን ውጪ በሁለቱ አገራት መካከል የሚደረጉት መደበኛ በረራዎች መቀጠላቸውን አረጋግጧል።
የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዘመናዊ ተዋጊ ድሮን መታጠቁን አስታወቀ
የsu-30 ተዋጊ ጀቶች እና የስትራቴጂክ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) የመጀመሪያ ዙር ርክክብ መከናወኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
ርክክቡ ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ “በአለማችን ላይ ተመራጭ የሆኑትን የsu-30 እና የስትራቴጂክ ሰው አልባ አውሮፕላን ባለቤት መሆናችን በሀገራችን ላይ ሊቃጡ የሚሞከሩ ጥቃቶችን ለማክሸፍ ወሳኝ ናቸው”
ብለዋል።
የ5ኛ ትውልድ አካል የሆኑት ዘመናዊ ተዋጊ አውሮፕላኖችና የስትራቴጂክ ስው አልባ አውሮፕላኖች አየር ሀይሉን የማዘመን አንዱ አካል መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ እንዳሉት፣
ተቋሙ የተረከባቸው ዘመናዊ የጦር ጀቶች በተመሳሳይ ጊዜ በአየርና በምድር ላይ ያለ የጠላት ታርጌትን ማውደም የሚችል ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የተረከበቻቸው ዘመናዊ የስትራቴጂክ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላኖች የጠላትን ዒላማ የማይስቱ ናቸው።
የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ለጠቅላይ ኤታማዦሩ ሹሙና ለእንግዶች አዲሱን su-30 ተዋጊ ጀት በማብረር የተለያዩ የአየር ላይ ትእይንቶችን አሳይተዋል።
ኢትዮጵያ በኢጋድ ስብሰባ እንደማትሳተፍ አስታወቀች
ኢትዮጵያ፤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግታት ድርጅት (ኢጋድ) በዛሬው ዕለት ጥር 8 ቀን 2016 ዓ/ም በሚያካሄደው ጉባዔ ላይ “በተደራራቢ መርሀ ግብር” ምክንያት መገኘት የማትችል መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል አስታውቃለች።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለጂቡቲ የውጭ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር እና ለኢጋድ በላከው ድብዳቤ “ኢጋድ ከጠራው ጉባኤ ቀደም በሎ ከተያዘው መርሃ ግብር ጋር የሚጋጭ መሆኑ እና የተቀመጠው ጊዜ አጭር መሆኑ ” ኢትዮጵያ በኡጋንዳ ካምፕላ
በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አስቸጋሪ ያደርገዋል ብሏል።
ይሁን እንጂ “ኢትዮጵያ ኢጋድ በሚመራበት ደምብ መሰረት በተለዋጭ ቀን ለመወያየት ዝግጁ ናት” ሲል ደብዳቤው አክሏል።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል በተፈጠረው ውዝግብ እና በሱዳን እየተካሄደ ባለው ግጭት ዙሪያ ለመመከር ቀነ ቀጠሮ መያዙ መዘገባችን ይታወሳል። የጁቡቲው ፕሬዝዳንትና የኢጋድ ሊቀመንበር
የሆኑት ኢስማዔል ጌሌ አባላቶቹ ጥር 9 በኡጋንዳ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ጥሪ አቀረበዋል።
በኦሮሚያ ክልል አዲስ በተዋቀረ ዞን ማህበራዊ አገልግሎት ተቋረጠ
ኦሮሚያ ክልል ከመዋቅር ጋ በተገናኘ ተቃውሞ ጎሮዶላ ወረዳ የተለያዩ የማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራ መስተጓጎሉ ትምህርትም አለመጀመሩ ተገለጸ ።
እስካሁን ትምህርት አለመጀመሩ የተነገረው ባለፈው ዓመት ኦሮሚያ ክልል በዘረጋው አዲስ የዞን መዋቅር በምስራቅ ቦረና ስር በተዋቀረው ጎሮዶላ ወረዳ ነው ። በዚህም ስጋት እንደገባቸው የተናገሩት ተማሪዎች እና የተማሪዎች ወላጆች ነገሩ እንዳሳሰባቸው
አስረድተዋል።
Support Reyot Media:
Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb
Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about
Follow us:
Twitter: @reyotmedia
Facebook: @ReyotMedia
Instagram: @reyot_media
TikTok: @reyotofficial
Threads: @reyot_media