Connect with us

Hi, what are you looking for?

News

የርዕዮት ዜናዎች፤ 10-ጥር-2016

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ በገለልተኛ ሀገራት 19ኛው ጉባኤ ላይ ተገኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እና የልዑካን ቡድናቸው በኡጋንዳ፣ ካምፓላ እየተካሄደ በሚገኘው የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥታት 19ኛው ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የልማት ፍላጎታቸውን ለማሟላት እየተቸገሩ መሆናቸውን እና ከባድ ፈተናዎች እንደሚገጥማቸው ገልጸዋል። ኢትዮጵያም ይህን ችግር ለመፍታት በሰላማዊና በጋራ ተጠቃሚነት እንዲሁም በድርድር መፍትሄ ለማግኘት ጥረት እያደረገች ነው ብለዋል።

ወደብ ለመጠቀም ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው ስምምነት ኢትዮጵያን ከሶማሊያ ጋር ውጥረት ውስጥ ማስገባቱን ተከትሎ የተጠራው የኢጋድ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ እንደማትሳተፍ መዘገባችን ይታወሳል።

የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማሊያን ሉአላዊነት እንዲያከብር ጠየቁ

በኡጋንዳ ኢንተቤ ልዩ ስብሰባቸውን ያካሄዱት የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት እጅግ እንዳሳሰባቸው በመግለጽ የሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንዲከበር አሳስበዋል። በተጨማሪም ማንኛው ስምምነት በሶማሊያ መንግስት ይሁንታ ላይ የተመሰረተ መሆን ይገባዋል ብለዋል።

ሁለቱ ሀገራት ግጭት የሚያባብሱ መልዕክቶችን ከማስተላለፍ እንዲቆጠቡ የጠየቀው ኢጋድ ገንቢ በሆኑ ንግግሮች ላይ እንዲያተኩሩም አሳስቧል።

በኢንተቤ በተካሄደው 42ኛው የኢጋድ መሪዎች ልዩ ስብሰባ ሌላኛው የመከረው አብይ ጉዳይ የሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ሲሆን ተፋላሚ ሀይሎች ግጭቶችን በማስቆም ወደ ውይይት እና ድርድር እንዲመጡ ጠይቋል።

እናት ፓርቲ መንግስት ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ ከፓን አፍሪካ አቀንቃኟ ኢትዮጵያ የማይጠበቅ ድርጊት ነው ሲል ወቀሰ

ኢዜማና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እንዲሁም አንዳንድ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነቱ የደገፉ ቢሆንም እናት ፓርቲ ግን ተቃውሟል።

እናት ፓርቲ፣ መንግስት፣ ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ ኢትዮጵያን ከመሰለች ጥንታዊት፣ ታሪካዊት እና የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ አገር የማይጠበቅ ድርጊት ነው ሲል ኮንኗል። ፓርቲው ይህን ያለው ዛሬ መንግሥት በሱማሊላንድ የባህር ኃይል ቤዝ ዙሪያ የተፈራረመውን የመግባቢያ ሰነድ መልሶ ሊያጤነው ይገባል ሲል ባወጣው መግለጫ ላይ ነው።

እናት ፓርቲ የፌደራል መንግሥቱ ከተደቀኑበት የውስጥ ችግሮች ትኩረትን ዘወር በማድረግ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ለመሥራት የሄደበት እርቀት ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታት ሶማሊያ ጀምሮ ከአፍሪካ አገራት እና ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ውጥረት እና ግጭቶች
ውስጥ ሊከተው እንደሚችል መገንዘቡን አመልክቷል። ስምምነቱ በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልልም ሌላ ጥያቄና ቀውስ በመጠንሰስ በአገር ውስጥ ቀውስ ሊፈጠር እንደሚችል የጠቆመው መግለጫው ከዚህ ችግር ባሻገር ከሶማሊያ ጋር የገባንበት ፍጥጫ ቀስበቀስ ወደ ኃይል አማራጭ አድጎ ጉዟችን ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሆን ትልቅ ስጋት አለኝ ብሏል።

ፓርቲው በመግለጫው የሶማሊያ መንግሥት ጉዳዩን አግዝፎ ወደ ኃይል ፍጥጫ ከመሻገር ይልቅ ሰከን ባለ መልኩ ጉዳዩን ተመልክቶ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔዎችን ብቻ በመከተል ስጋቱን ለመቅረፍ እንዲሰራ አሳስቦ ስምምነቱን ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተደረገ የሚገኘውን ጥቃት አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልጿል።

ፓርቲው በዚሁ መግለጫው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ሞክር ቤት ከአንድ ሳምንት በፊት መንግሥት ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመውን የመግባቢያ ሰነድ አስመልክቶ ሁሉም ፓርቲዎች ያለልዩነት እንደደገፉት አድርጎ የሰጠው መግለጫ ትክክል አይደለም ሲል ተችቷል።

በመጨረሻም እናት ፓርቲ በጉዳዩ ላይ ያነሳው የልዩነት ሀሳብ በመግለጫው ሊጠቀስ ሲገባ ካለልዩነት በአንድ ድምጽ እንደተደገፈ ተደርጎ መቅረቡ ትክክለኛ አለመሆኑን እወቁልኝ ብሏል።

ኢሰመኮ ፖሊስ ሰላማዊ ሰዎችን መግደሉን ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጋሞ ዞን፣ በቆላ ሻራ ቀበሌ ውስጥ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በቀበሌው ነዋሪዎች መካከል የነበረውን አለመግባባት ተከትሎ ነዋሪዎች መሞታቸውን ንብረት መውደሙን አስታውቋል።

ለሟቾች ቤተሰቦች እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እንዲሁም ንብረታቸው ለወደመባቸው ሰዎች፣ ለደረሰባቸው ጉዳት ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ እንዲከፈል ሲል ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ “ተጠያቂነትን ከማረጋገጥና የተጎዱትን ከመካስ በተጨማሪም ለዚህና ተመሳሳይ ግጭቶች ምክንያት የሆነው የአካባቢ አስተዳደር መዋቅር ጥያቄና ውዝግብ ነዋሪዎችን ተአማኒ በሆነ መንገድ
ባሳተፈ ሰላማዊ ውይይት አፋጣኝ መፍትሔ ይሻል” ማለታቸውንም አመላክቷል፡፡

ዩናይትድ ኪንግደም የኤርትራ አምባሳደርን ልታባርር ነው

የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በለንደን የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት እስጢፋኖስ ሃብተማርያም ከአገሩ እንዲወጡ ማዘዙን ተሰማ።

ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ለሚሆን ጊዜ ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ኤርትራ እና ዩናይትድ ኪንግደም የአምባሳደሩን መባረርን በተመለከተ በይፋ የሰጡት መግለጫ የለም።

በአሁኑ ወቅት በለንደን የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ድረ-ገጽ እንደሚያመለክተው የአምባሳደሩን ቦታ በመሸፈን የኤምባሲው ከፍተኛ ተጠሪ በመሆን የሚሠሩት ሳሌህ አብዱላህ ናቸው።

የዩኬ መንግሥት አምባሳደር እስጢፋኖስ ሃብተማርያም ላይ ከአገር እንዲወጡ የወሰደው እርምጃ፣ ኤርትራ ቀደም ብሎ ለወሰደችው ተመሳሳይ ውሳኔ ምላሽ መሆኑን ተነግሯል።

Support Reyot Media:

Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb

Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about

Follow us:

Twitter: @reyotmedia

Facebook: @ReyotMedia

Instagram: @reyot_media

TikTok: @reyotofficial

Threads: @reyot_media


Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Trending

You May Also Like

Sticky Post

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ትውልድ ይፈርድብናል አሉ በትናትናው እለት በተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተገኝተው ንግግር ያሰሙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመረቀው ሙዚየም አገርን ለሆነው ላልሆነውማናወጥ፤...

Sticky Post

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች እና የህወሓት ከፍተኛ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ተገናኙ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል...

Sticky Post

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹም ሽር አደረጉ በዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ የሶስት ሚኒስትሮች ሹመት ጸደቀ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሥልጣን የተሰናበቱትን ምክትል ጠቅላይ...

Sticky Post

ምክር ቤቱ ይፋዊ ይቅርታ ለመጠየቅ መቐለ ገባ በ ሸኽ ሓጂ ሙሐመድ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን...