Connect with us

Hi, what are you looking for?

News

የርዕዮት ዜናዎች፤ 14-ጥር-2016

አቶ ጌታው ረዳ ስብሰባችንን እናሳጥራለን አሉ

የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ለወራት በዝግ ስብስባ መቀመጣቸው ያጋጠመውን ከፍተኛ ተቃውሞ ተከትሎ በማይ ጨው ከተማ የጥምቀትን በዓል ለማበር የተገኙት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ስብሰባችንን በማሳጠር የህዝባችንን እድሜ እናራዝማለን ብለዋል፡፡

አስተዳደራቸው በብሄራዊ ጥቅም ላይ መሰረት ያደረገ ፖሊስና ስትራቴጂ በመከተል አጋጥሞ ያለው የረሀብ አደጋ ለመፍታት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የረሀብ አደጋው የ1977ቱን ታሪክ የሚደግም መሆኑን አቶ ጌታቸው መናራቸው አይዘነጋም፡፡

የሰራተኛና ክህሎት ሚኒስቴር ለትግራይ ለስራና ምርትን ለማሳደግ 300 ሚልዮን ብር መድቧል ተባለ

የሰራተኛና ክህሎት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠርና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማነቃቃት ያስችላል የተባለዉን የ300 ሚሊዮን ብር የድጋፍ ፓኬጅ ይፋ ማድረጉን ተሰምቷል።

ከተያዘው ገንዘብ ውስጥ 100 ሚሊዮን ብር ለክልሉ ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ይውላል የተባለ ሲሆን 200 ሚሊዮን ብር ደግሞ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን ለማነቃቃት የሚውል ነው።

የሰራተኛና ክህሎት ሚኒስተር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል መንግስት እና የአለም ባንክ እራሳቸውን እና ማህበረሰባቸውን ለማሻሻል በኢኒሼቲቭ ከሚሳተፉት ሁለት ሺህ ወጣቶች ለእያንዳንዳቸው 50,000 ብር ከድጋፍ ፓኬጅ እንደሚረከቡ ተናግረዋል።

ሚኒስቴሩ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት ከመጀመሩ በተጨማሪ አነስተኛና መካከለኛ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎችን ለማነቃቃት 200 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል። የተመደበው ድጋፍ የማኑፋክቸሪንግ ሴክተሮችን በጊዜያዊ አስተዳደሩ ሶስት ሺህ
ሰራተኞችን ለማነቃቃት ይውላል ተብሏል፡፡

መንግሥት በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ለየሚገኙ አካባቢዎች የመንግስት ሰራተኞችን መደበ

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ስር በሚገኙ እና በአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) በተያዙ የአበርገሌ ወረዳ 12 ቀበሌዎች ውስጥ የመንግሥት ሠራተኞች በድጋሚ ማሰማራት እንደተጀመረ ተገለጸ፡፡

በሁለቱ ወገኖች ስምምነት መሠረት የአካባቢው የመንግሥት ሠራተኞች ወደ አካባቢዎቹ ቢመለሱም የቀበሌዎቹ “ፖለቲካዊ እና የፀጥታ አስተዳደር ለጊዜው” በታጣቂዎቹ ስር እንደሚቆይ የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አስታውቋል።

በዋግ ኽምራ ብሔሰረብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ ውስጥ ወደሚገኙት 12 ቀበሌዎች የመንግሥት ሠራተኞችን የመመለሱ ሥራ የተጀመረው የአማራ ክልል እና አዴን በፈጸሙት የሰላም ስምምነት መሠረት መሆኑን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለሙ ክፍሌ
ለቢቢሲ ገልጸዋል።

የብልጽግና መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር ለሶስተኛ ጊዜ ለድርድር እንዲቀመጥ ሊደረግ ነው ተባለ

በታንዛንያ በሁለት ዙር ተካሂዶ ባለቀ ሰዓት የተሰተጓጎለውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትንና የመንግስትን ድርድር ለሶስተኛ ዙር ለማስቀጠል እንዲሁም የአማራ ክልል ፋኖ ታጣቂዎችን ወደ ድርድር ለማምጣት በአሜሪካ እና በአውሮፓ ህብረት በኩል የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ተዘገበ፡፡

የፌደራሉ መንግስትና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ድርድር በስልጣን ድልድልና በአሸባሪነት ፍረጃ እንዲሁም ጉልህ ባልሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ በተነሱ አለመግባባቶች ከሁለት ወራት በፊት ሳይሳካ መቅረቱ ይታወሳል።

የአሜሪካ መንግስት ዋና አደራዳሪ ማይክ ሀመር ከኢጋድና የአፍሪቃ ህብረት ጋር በመሆን ድርድሩን ለማስቀጠል የሚያስችል ውይይት ከመንግስት ጋር ለማድረግ እና የፕሪቶሪያውን ስምምነት አተገባበር ለመገምገም ባለፉት ቀናት ወደ አዲስ አበባ አቅንተው ነበር። በቆይታቸውም ድርድሩን ማስቀጠል የሚያስችሉ ዝርዝር ጉዳዮችን ከሚመለከታቸው ጋር
መወያየታቸውን ተነግርዋል፡፡

በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች ጋር ድርድር ማድረግ የሚቻልበት ጉዳይ ላይ ባለፉት ሁለት ወራት በአሜሪካ መንግስትና በአውሮፓ ህብረት እንዲሁም በእንግሊዝ መንግስት በኩል ጥረቶች ሲደረጉ መሰንበታቸው ይታወሳል።

በኦሮሚያ መንበረ ጴጥሮስ የተባለ ሲኖዶስ መመስረቱ ተሰማ

በኦሮሚያ መንበረ ጴጥሮስ የተባለ ሲኖዶስ መመስረቱን ዛሬ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተነግሯል።

ጋዜጣዊ መግለጫውን በንባብ ያቀረቡትየምዕራብ ወለጋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በቋንቋችን ለመማር እና በነጻነት ለማምለክ ለዘመናት ተከልክለናል ብለዋል።

በመሆኑም በቤተክርስትያኗ ዶግማና ቀኖና መሰረት የኦሮሚያና ብሄሮች ሲኖዶስ መቋቋሙንና ብፁሃን አባቶች መሾማቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ጉዳዩ በእርቅ እንዲያልቅ ለማድረግ ተወስኖ እኛም ተቀብለናል፤ ይሁንና ጥያቄያችን ተዳፍኖ ቀርቷል ያለው መግለጫ በማከል ለትግራይና ለአማራ ህዝብ ሲኖዶስ ተፈቅዶ የኦሮሞ ህዝብ በራሱ ቋንቋ ማምለክ ለምን ይከለከላል ሲል ይጠይቃል።

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምንም አይነት ቀለም ያለው ባንዲራም ሆነ ምልክት ስለሌላት በኦሮሚያ ምድር ላይ የማንንም የፖለቲካ ፖርቲ ባንዲራ በቤተክርስትያን ሽፋን እንዳይውለበለብ፣ እንዳይሰቀል፣ እንዳይቀባ በመሳሰብ የኦሮቶዶክስ ቀለሟና ባንዲራዋ የክርስቶስ መስቀል ብቻ እንደሆነ መግለጫው ይናገራል፡፡

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በብዛት ከሚታሰሩባት አገርት አንዷ ተባለች

በአፍሪካ በ2023 በርካታ ጋዜጠኞች ከታሰሩባቸው ሶስት ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ሲፒጄ አስታወቀ፡፡

ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት 2023 በአፍሪካ በርካታ ጋዜጠኞች ከታሰሩባቸው ሶስት ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ሲፒጄ ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ።

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር በአፍሪካ ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ያስታወቀው የጋዜጠኞች ተቆርቋሪ ተቋሙ ሲፒጄ ኤርትራ እና ግብጽ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ መያዛቸውን አመላክቷል።

በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ብዛት ስምንት መሆኑን የጠቆመው ሲፒጄ በሀገሪቱ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት ለእስር የተዳረጉት ጋዜጠኞችም በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተነሳውን ግጭት በተመለከተ ይዘግቡ የነበሩ መሆናቸውን አስታውቋል።

በኤርትራ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ብዛት 16 መሆኑን እና በግብጽ ደግሞ 13 ጋዜጠኞች ለእስር መዳረጋቸውንም ጠቁሟል።

Support Reyot Media:

Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb

Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about

Follow us:

Twitter: @reyotmedia

Facebook: @ReyotMedia

Instagram: @reyot_media

TikTok: @reyotofficial

Threads: @reyot_media

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Trending

You May Also Like

Sticky Post

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ትውልድ ይፈርድብናል አሉ በትናትናው እለት በተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተገኝተው ንግግር ያሰሙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመረቀው ሙዚየም አገርን ለሆነው ላልሆነውማናወጥ፤...

Sticky Post

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች እና የህወሓት ከፍተኛ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ተገናኙ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል...

Sticky Post

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹም ሽር አደረጉ በዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ የሶስት ሚኒስትሮች ሹመት ጸደቀ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሥልጣን የተሰናበቱትን ምክትል ጠቅላይ...

Sticky Post

ምክር ቤቱ ይፋዊ ይቅርታ ለመጠየቅ መቐለ ገባ በ ሸኽ ሓጂ ሙሐመድ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን...