Connect with us

Hi, what are you looking for?

News

የርዕዮት ዜናዎች፤ 17 – ጥር – 2016

ብልጽግና አቶ ደመቀ መኮንን አሰናበተ

የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ ብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ከፓርቲ ኃላፊነታቸው መሰናበታቸው ተገለጸ።

አቶ ደመቀን በመተካትም የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን ለረጅም ዓመታት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ ነበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታን የያዙት። በቀድሞው ኢህአዴግ እና በአሁኑ ብልጽግና ፓርቲው ውስጥ ቁልፍ ሥልጣንን ይዘው የቆዩት አቶ ደመቀ መኮንን የብአዴን ሊቀመንበር ሲሆኑ በህዳር 2005 ዓ.ም የኢህአዴግ ምክትል ሊቀምንበር ሆነው ከተመረጡበት ጊዜ ጀምሮ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት እያገለገሉ ነበር።

የአማራ ክልል የአፈር ማዳበሪያ ላሰራጭ ነው አለ

የአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት ለ2016/17 ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ለአማራ ክልል አርሶአደሮች በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው ሲል ገልጿል።

የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ በበኩላቸው የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ተፈፅሞ በአግባቡ ተጓጉዞ በወቅቱ ከአርሶአደሩ እንዲደርስ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በ2015/2016 ምርት ዘመን በውጊያ ምክንያት የክልሉ አርሶ አደር ግብርናዉን ማስቀጠል ሳይችል መቅረቱ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።

ሶማሊላንድ መሬቴን ለኢትዮጵያ ያከራየሁት ለንግድ አይደለም አለች

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ባሂ ከሀገራቸው ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (SLNTV) ጋር ባካሄዱት ቃለምልልስ ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ በሊዝ የምትሰጣት መሬት ለባህር ሀይሏ ብቻ የምትጠቀምበት እንጂ ለንግድ እንቅስቃሴ የሚያገልግል አይደለም አሉ።

ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ስለተፈረመችው የመግባቢያ ሰነድ ባብራሩበት ወቅት እንደተናገሩት በመግባቢያ መሰረት ኢትዮጵያ ለባህር ሀይሏ የምትጠቀምበትን የባህር ላይ ዳርቻ ከሶማሊላንድ እንደምታገኝ እና ሶማሊላንድ በምትኩ
ወዲያውኑ ሉአላዊ ሀገር ሁና በኢትዮጵያ እውቅና እንደሚሰጣት ገልጸዋል።

ሁለቱም ጉዳዮች በተመሳሳይ ግዜ ተፈጻሚ እንደሚሆኑ በተፈረመው ሰነድ ላይ መቀመጡን ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያ ለገቢ እና ወጪ ንግዷ የበርበራ ወደብን ብቻ ትጠቀማለች ሲሉ አብራርተዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ በአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ሥር በሶማሊያ የተሠማሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ትናንት ከኪሲማዩ ወደብ አከባቢ መውጣታቸው ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ወታደሮች ማድሃማቶ ከተባለ የህብረቱ የሰላም ተልዕኮ ወታደራዊ ጦር ሠፈር የወጡት፣ ተልዕኮው በአገሪቱ የተሠማሩ ወታደሮችን ደረጃ በደረጃ ለማስወጣት በጀመረው ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር መሠረት ነው። የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ወታደሮች ያስረከቡት የኪሲማዩን አውሮፕላን ማረፊያ ይጠብቅ የነበረውን ጦር ሠፈር ነው።

የትግራይ ክልል የተሻሻለውን ካሪኩለም እንደማይከተል አስታወቀ

የትግራይ ክልል ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር የተሻሻለውን ሥርዓተ ትምህርት እንደማይከተሉ ተገለጸ።

ለአሁኑ እና ለቀጣይ የትምህርት ዘመን በትግራይ ለሚማሩ ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከቀድሞው ሥርዓተ ትምህርት ጋር የሚጣጣም መሆኑን የትምህርት ኃላፊዎች ገልጸዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ትምህርት ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ሸዋረጌት ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ውሳኔው የተገኘው በሚኒስቴሩ እና በትግራይ ትምህርት ቢሮ መካከል ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ ነው።

ሚኒስቴሩ ከዚህ የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የሀገሪቱ የመንግስትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አዲሱን ስርዓተ ትምህርት በመተግበር ላይ ይገኛል።

በሸገር ከተማ የታሰሩ የሃይማኖት አባቶች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በ“መንበረ ጴጥሮስ” ስም የሚጠራ “የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መሥርተናል” በሚል መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ የታሰሩት የሃይማኖት አባቶች፣ ዛሬ ፍርድ ቤት እንደቀረቡና የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንደተጠየቀባቸው
ጠበቃቸው ተናገሩ፡፡

ከእንቅስቃሴው ጋራ በተያያዘ የታሰሩት የሃይማኖት አባቶች እና አገልጋዮች ቁጥር ዘጠኝ መድረሱንም፣ ከ“መንበረ ጴጥሮስ” ምስረታ አስተባባሪዎቹ አንዱ እንደሆኑ የጠቀሱት ዲያቆን አክሊሉ ዓለሙ ናቸው።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በኩልም፣ እስከ አኹን ጉዳዩን አስመልክቶ የወጣ ይፋዊ መግለጫ የለም።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የተከተቡ ህጻናት በኩፍኝ በሽታ እየሞቱ መሆኑን ተገለጸ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃድያ ዞን ምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ በተቀሰቀሰ የኩፍኝ በሽታ ሕጻናት ለሞት እየተዳረጉ ነው ተባለ።

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በሽታው በወረዳው መታየት የጀመረው ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ ቢሆንም ሕጻናት በዚሁ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፍ የጀመረው ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ነው።

አሁን በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ሕጻናት እየሞቱ፤ በርካቶችም በበሽታው እየተያዙ መሆኑንም አክለዋል። የሃድያ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታከለ ኦልበሞ በሽታው መከሰቱንና ሰዎችም መሞታቸውን አረጋግጠዋል።

አቶ ታከለ እንደሚሉትም በበሽታው ከተያዙት 61 በመቶው ክትባት የተከተቡ ቢሆንም መከላከያ ክትባት ተከትበው ሳለ በበሽታው ለመያዝ ያበቃቸው ምን እንደሆነ ለመናገር
እንደሚቸገሩም አስረድተዋል። እንዲያም ሆኖ በአሁኑ ወቅት በበሽታው ለተያዙት ህክምና እየተሰጠ እንደሆነ እና በሽታው እንዳይስፋፋ ለማድረግም የቫይታሚን ኤ ዕደላን ጨምሮ የተለያዩ ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል።
Support Reyot Media:

Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb

Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about

Follow us:

Twitter: @reyotmedia

Facebook: @ReyotMedia

Instagram: @reyot_media

TikTok: @reyotofficial

Threads: @reyot_media


Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Trending

You May Also Like

Sticky Post

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ትውልድ ይፈርድብናል አሉ በትናትናው እለት በተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተገኝተው ንግግር ያሰሙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመረቀው ሙዚየም አገርን ለሆነው ላልሆነውማናወጥ፤...

Sticky Post

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች እና የህወሓት ከፍተኛ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ተገናኙ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል...

Sticky Post

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹም ሽር አደረጉ በዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ የሶስት ሚኒስትሮች ሹመት ጸደቀ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሥልጣን የተሰናበቱትን ምክትል ጠቅላይ...

Sticky Post

ምክር ቤቱ ይፋዊ ይቅርታ ለመጠየቅ መቐለ ገባ በ ሸኽ ሓጂ ሙሐመድ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን...