Connect with us

Hi, what are you looking for?

News

የርዕዮት ዜናዎች፡ 28 – ጥር – 2016

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በረሀብ የሞተ ሰው የለም አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማራሪያ በአገሪቱ በረሀብ የሞተ ሰው የለም ብለዋል፡፡

በተጨማሪም “መንግሥት ለድርቅ ትኩረት አልሰጣም ” የሚባለውን በማጣጣል በርሃብ ሰው እንዳይሞት በቢሊዮንሚቆጠር ገንዘብ እያወጣ ነው ብለዋል።

እርሳቸው ይህን ቢሉም መንግስታዊ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ባለፈው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት በአማራና ትግራይ ክልሎች በድምሩ 372 ሰዎች በረሀብ መሞታቸው ይፋ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

መንግስት ዲሞክራሲ አብዝቶ ስለሰጠ ስርዓት አልበኝነት መስፋፋቱን ጠቅላይ ሚኒሰተሩ ተናገሩ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሀገራዊ ሰላምና ፀጥታ ጋር በተያያዘ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት “ስርዓት አልበኝነት” የተበራከተው፤ በሀገሪቱ “ዲሞክራሲን የመለማመድ” እና “ነጻነትን የማስተዳደር ችግር” በመኖሩ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መንግስታቸው “ስድብ እና ጥፋት” ያሉትን አብዝቶ እንደታገሰ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስተሩ “ሕግ የማስከበር” እንደሚቀጥል ጨምረው አስጠንቅቀዋል። ሆኖም ሕግ ለማስከበር ስንሰራ በየአንዳንዷ ሰከንድ ለሠላም ዝግጁ የሆነ ኃይል ካለ በራችን ክፍት ነው ” ያሉ ሲሆን “ለውይይት ለሠላም፣ ለንግግር ክፍት ነን። ሕግ የማስከበሩን ሥራ ከንግግር እና ከውይይት ውጭ እንዲሆን አንፈልግም ” ብለዋል።

የትግራይ ክልል የፌደራል መንግስትን ከሰሰ

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የብልጽግና መንግስት ፀረ ፕሪቶርያ አቋም ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን እያበረታታ ነው ሲል ከሰሰ፡፡

የፌድራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከፕሪቶርያ ስምምነት ጋር በተያያዘ ባወጣው መግለጫ ዙሪያ የትግራይ ክልል መንግስት ግዜያዊ አስተዳደር በፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በሰጠው ምላሽ ከፕሪቶርያ ስምምነት አፈፃፀም ጋር በተያያዘ የተሰሩና እስካሁንም ባልተሰሩ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት ቀጠሮ መያዙን ግዜያዊ
አስተዳደሩ በመግለጫው ጠቁሞ ከተያዘዉ ቀጠሮ በፊት መግለጫ መውጣቱ ተገቢ ነዉ ብሎ እንደማያምን አስታውቋል።  

ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር በተያያዘ የፌዴራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው ባነሳቸው ጉዳዮችን በሚመለከት
ማብራርያ ሰጥቷል።

በተለይ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት “አከራካሪ ቦታዎች” ሲል በገለጻቸው ቦታዎች ዙሪያ ጉዳዩን በሪፈረንደም ለመፍታት መረዳዳት ተደርሶ ነበር መባሉ ፍፁም የተሳሳተ ነው ሲል የተቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከተሰጠን ስልጣን ውጪ የሆነ ተግባር ነው፣ ተቀባይነት የለውም ብሏል።

ከተፈናቃዮች መመለስ ጋር ተያይዞ “ትክክለኛ ተፈናቃዮች ተመልሰዋል” በሚል ለቀረበው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ ክፍል ጋር በተያያዘ አደገኛ ትንታኔ ነው ሲል ገልጾ በጉልበት የሃገሪቱ ካርታ ለመቀየር የፌዴራል መከላለያ ሆነ የጎርቤት ሃገራትን አቅም ተጠቅሞ የተደረገን አውዳሚ እንቅስቃሴ ሕጋዊ ሽፋን ለመስጠት የሚያግዝ ነው ሲል ተችቷል።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው በትግራይ ከተካሄደው ጦርነት ጋር የተገናኙ “ወንጀለኞችን” ተጠያቂ አድርጊያለሁ፣ “ተገቢውን እርምጃም” ወስጃለሁ ማለቱን በተመለከተ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በመግጫው ፍትህ የማረጋገጥ ተግባር የዘመቻ ጉዳይ እንዳልሆነ ታውቆ ሁሉም ሊሰራበት የሚገባ ነው ሲል ገልጿል።

ጸረ-ፕሪቶርያ አቋም ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በተሳሳተ አቋማቸው እንዲገፉበት የሚያበረታታ መግለጫ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን ነው ሲሉ የፌዴራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት መግለጫን ተችቷል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን አስታውቃለች።

ቤተክርስቲያን ፤ ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና ሰጥተው እንደነበር አስታውሳለች። ብፁዕነታቸው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደረሰው ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በአየር መንገድ አቀባበል ለማድረግ በተገኘበት ወቅት እንዳይገቡ መከልከላቸውን ማረጋገጡን ቤተክርስቲያኗ የገለጸች ሲሆን የመንግስት አካል የቤተክርስትያኗ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አገር እንዲገቡ እንዲፈቀድላቸው እንዲደርግ ” ስትል ጥሪዋን አስተላልፋለች።

ሶማሊያ ውስጥ ቢያንስ 7 ኢትዮጵያውያን ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ

በደቡባዊ ሶማሊያ በምትገኘው ጌዶ ክልል ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ ሰባት ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ በርካቶች ስጋት ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ።

በሶማሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ከኬንያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው በለደሀዎ ከተማ በተፈጸመው ጥቃት ኢትዮጵያውያን ስጋት ላይ እንደሆኑና በርካቶች ወደ አገር ቤት መመለስ ይፈልጋሉ ብሏል።

“ከተገደሉት መካከል ሁለቱ ሕጻናት ሲሆኑ፣ እናት እና አባቷ ተገድለውባት ብቻዋን የቀረች ሕጻንም አለች” ያሉት የማህበረሰቡ መሪ፣ የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች መርዶውን እንዳልሰሙ እና እስከ ሰኞ ከሰዓት በኋላ ቀብራቸው አልተፈጸመም ያሉ ሲሆን አክለውም፤

“የተገደሉት ሰዎች ወደ አገራቸው ተመልሰው በሥነ ሥርዓት ቀብራቸው እንዲፈጸም እንፈልጋለን። መንግሥት ይህን ማድረግ ይችላል። ለተገደሉትም ፍትሕ እንዲሰፍንም እንፈልጋለን።”

ከዚህ ግድያ ቀደም ብሎ በከተማዋ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ ግድያ መፈጸሙን የሚናገሩት የማኅበረሰብ መሪው በዚህ ሳቢያ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለስ እንደሚፈልጉ እና መንግሥትም ሆነ የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል።

እስካሁን በኢትዮጵያውያኑ ላይ ከተፈጸመው ጥቃት ጀርባ ማን እንዳለ የታወቀ ነገርም ሆነ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የለም።

Support Reyot Media:

Go Fund Me: https://gofund.me/afe7b8cb

Patreon: https://www.patreon.com/reyot/about

Follow us:

Twitter: @reyotmedia

Facebook: @ReyotMedia

Instagram: @reyot_media

TikTok: @reyotofficial

Threads: @reyot_media

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Trending

You May Also Like

Sticky Post

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ትውልድ ይፈርድብናል አሉ በትናትናው እለት በተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተገኝተው ንግግር ያሰሙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመረቀው ሙዚየም አገርን ለሆነው ላልሆነውማናወጥ፤...

Sticky Post

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች እና የህወሓት ከፍተኛ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ተገናኙ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል...

Sticky Post

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹም ሽር አደረጉ በዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ የሶስት ሚኒስትሮች ሹመት ጸደቀ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሥልጣን የተሰናበቱትን ምክትል ጠቅላይ...

Sticky Post

ምክር ቤቱ ይፋዊ ይቅርታ ለመጠየቅ መቐለ ገባ በ ሸኽ ሓጂ ሙሐመድ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን...